እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው?

ጥያቄ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው? መልስ፤ ለማያምኑት እግዚአብሔርን መፍራት የእግዚአብሔር ፍርድን መፍራት እና የዘለአለም ሞት ይህም ዘላለማዊ ከእግዚአብሔር መለየት ነው (ሉቃስ 12፡5, ዕብ 10:31)፡፡ ለአአማኞች እግዚአብሔርን መፍራት በጣም የተለየ ነገር ነው፤ የአምልኮ ፍርሃት እግዚአብሔርን ማክበር ነው ዕብራውያን 12: 28-29 ለዚህ ጥሩ መግለጫ ነው፡- ‹‹ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ…

ጥያቄ፤

እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው?

መልስ፤

ለማያምኑት እግዚአብሔርን መፍራት የእግዚአብሔር ፍርድን መፍራት እና የዘለአለም ሞት ይህም ዘላለማዊ ከእግዚአብሔር መለየት ነው (ሉቃስ 12፡5, ዕብ 10:31)፡፡ ለአአማኞች እግዚአብሔርን መፍራት በጣም የተለየ ነገር ነው፤ የአምልኮ ፍርሃት እግዚአብሔርን ማክበር ነው ዕብራውያን 12: 28-29 ለዚህ ጥሩ መግለጫ ነው፡- ‹‹ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።›› ይህ አክብሮትና አድናቆት ለክርስቲያኖች እግዚአብሔርን መፍራት ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ለሆነው አጽናፈ ዓለም ፈጣሪ ራስን አሳልፎ ለመስጠት ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡

ምሳሌ 1 7 ‹‹ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው››ይላል፡፡ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ እስካልተረዳን እና እርሱን ለእርሱ ያለንን አክብሮት ማሳደግ እስካልቻልን ድረስ እውነተኛ ጥበብ የለንም፡፡ እውነተኛ ጥበብ የሚመጣው እግዚአብሔር ማን እንደሆነና እርሱ ቅዱስ እና ጻድቅ መሆኑን በማወቅ ብቻ ነው. ዘዳግም 10፡12, 20-21 እንዲህ ይላል- ‹‹እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው?አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።ዓይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቆች የሚያስፈሩትንም ነገሮች ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱም አምላክህ ነው።››እግዚአብሔርን መፍራት በመንገዱ ለመጓዝ እርሱን ለማገልገል እና እርሱን ለመውደድ መሰረት ነው፡፡

አንዳንዶች አማኞች እግዚአብሐየርን መፍራት “እግዚአብሔርን ማክበር” በማለት ይተረጉማሉ፡፡ ምንም እንኳን አክብሮት የሚለው በእርግጥ እግዚአብሔርን መፍራት በሚለው ጽንሰ-ሀሳብ ውስጥ ተካትቷል፤ ከላዚያ በላይ የሚለው አለ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ፍርሃት ለአማኝ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚጠላ እና በኃጢአተኛው ላይ ያለውን ፍርድ በመፍራት በአማኝ ሕይወት ውስጥ መፍራትንም ይጨምራል፡፡ ዕብራውያን 12፡5-11 የሚገልጸው እግዚአብሔር የአማኙን ተግሣጽ ነው፤ በፍቅር ተሠርቶአል (ዕብራውያን 12፡ 6), አሁንም ቢሆን በጣም የሚያስፈራ ነገር ነው፡፡ እንደ ልጆቻችን ከወላጆቻችን ተግሣጽ መፍራት አንዳንድ የክፉ ድርጊቶችን እንዳናደርግ እንዳስቻለን ግልጽ ነው፡፡ ከእግዚአብሔርም ጋር ባለን ግንኙነትም ረገድም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው፡፡ የእርሱን ተግሣጽ መፍራት አለብን እና ስለዚህ እሱን በሚያስደስት መንገድ ሕይወታችንን ለመኖር መፈለግ አለብን፡፡

አማኞች እግዚአብሔርን መፍራት አይኖርባቸውም፡፡ እርሱን ለመፍራት ምንም ምክንያት የለንም፡፡ ምንም ነገር ከእርሱ ፍቅር እንዳይለየን የገባን ቃል አለን (ሮሜ 8፡38-39)፡፡ እርሱ ፈጽሞ እንደማይተወን ቃል ገብቶልናል ተናግሮና (ዕብ 13፡5)፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በህይወታችን አኗኗር ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ስለሚችል ለእሱ ከፍተኛ አክብሮት ማሳየትን ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት እርሱን ማክበር እርሱን መታዘዝ ለእርሱ ቅጣት ‹‹ዲሲፕሊን›› መገዛት እና በአክብሮት ማምለክ ነው፡፡

[English]



[ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ]

እግዚአብሔርን መፍራት ምን ማለት ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.