የክርስቲያኖች ህልም ትርጓሜ? ህልምህ ከእግዚአብሔር ነው?

ጥያቄ፤ የክርስቲያኖች ህልም ትርጓሜ? ህልምህ ከእግዚአብሔር ነው? መልስ፤ GotQuestions.org/Amharic የክርስቲያኖች የህልም ትርጓሜ አገልግሎት አይደለም፡፡ ህልምን አንተረጉምም፡፡ በአጽንኦት እናምናለን የግለሰቦች ህልም እና የህልሞቹ ትርጉም በእግዚአብሔርና በግለሰቡ መካከል ነው የሚሆነው፡፡ በቀደመው ጊዜ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በህልም ይናገር ነበር፡፡ ለምሳሌ፡ ዮሴፍ የያዕቆብ ልጅ (ዘፍ 37፡5-10) ዮሴፍ የማሪያም ባል (ማቲ 2:12–22); ሰለሞን (1 ነገ 3:5–15); ሰለሞን እና ሌሎችም (ዳን…

ጥያቄ፤

የክርስቲያኖች ህልም ትርጓሜ? ህልምህ ከእግዚአብሔር ነው?

መልስ፤

GotQuestions.org/Amharic የክርስቲያኖች የህልም ትርጓሜ አገልግሎት አይደለም፡፡ ህልምን አንተረጉምም፡፡ በአጽንኦት እናምናለን የግለሰቦች ህልም እና የህልሞቹ ትርጉም በእግዚአብሔርና በግለሰቡ መካከል ነው የሚሆነው፡፡ በቀደመው ጊዜ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በህልም ይናገር ነበር፡፡ ለምሳሌ፡ ዮሴፍ የያዕቆብ ልጅ (ዘፍ 37፡5-10) ዮሴፍ የማሪያም ባል (ማቲ 2:12–22); ሰለሞን (1 ነገ 3:5–15); ሰለሞን እና ሌሎችም (ዳን 2:1; 7:1; ማቲ 27:19). በነብዩ በኢዩኤልም የተነገረ ትንቢት አለ (ኢዩ 2:28), በሐዋሪያው ጴጥሮስ ተጠቅሶአል ሥራ 2፡17 እግዚአብሔር ህልምን እንደሚጠቀም ተጠቅሶአል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከፈለገ በህልም ይናገራል፡፡

ሆኖም በአምሮአችን ማስቀመጥ ያለብን መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ነው፤ ከአሁን እስከ ዘልአለም ለማወቅ የምንፈልገው ሁሉ በቃሉ ተገልጾአል፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር ተአምራትን አያደርግም ማለት አይደለም ወይም ዛሬ በህልም አይናገርም ማለት አይደለም ግን እግዚአብሔር የሚናገረው የተኛውም በህልምም ሆነ በራዕይ ወይንም ‹‹በለሆሳስ ድምጽ›› እግዚአብሔር በቃሉ ከገለጸው ጋር ሙሉ ለሙሉ የሚስማ መሆን አለበት፡፡ ህልም የእግዚአብሔርን ቃል አይተካም፡፡

ህልም ቢኖርህና እና እግዚአብሔር እንደሰጠህ ቢሰማህ በጸሎት በቃሉ ፈትነው እግዚአብሔርም የተናገርህ ከቃሉ ጋር የሚስማማ መሆኑን አረጋግጥ፡፡ በጸሎት ወስጥ እግዚአብሔር ስለህልም እየተናገረግ ከሆነ አስተውል (ያዕ 1፡5)፡፡፡ በቃሉ ማንኛውም ሰው ህልምን ቢለማመድ እግዚአብሔር የሕልሙ ትረጓሜ ግልጽ ያደርጋል፤ ለግለሰቡ በቀጥታ ይሁን ወይንም በሌላ መልዕክተኛ (ዘፍ 40፡5-11፤ ዳን 2፡45፤ 4፡19) እግዚአብሔር ለእኛ ሲናገረን መልዕክቱ ለእኛ ግልጽ እና የምንረዳው እንደሚሆን እርግጥ ነው፡፡

[English]



[ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ]

የክርስቲያኖች ህልም ትርጓሜ? ህልምህ ከእግዚአብሔር ነው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.