ደኅንነት ምንድነው? የክርስቲያን ዶክትሪን ስለ ደኅንነት ምንድነው?

ጥያቄ፤ ደኅንነት ምንድነው? የክርስቲያን ዶክትሪን ስለ ደኅንነት ምንድነው? መልስ፤ ደኅንነት ከአደጋ ወይም ከመከራ መውጣት/መታደግ ማለት ነው። ማዳን፣ መታደግ ወይም መጠበቅ ማለት ነው። ቃሉ የድልን፣ የጤንነትን፣ ወይም የመጠበቅን ሐሳብ ይዟል። አንዳንድ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የዳነ ወይም ደኅንነት የሚሉትን ቃላት ጊዜያዊ፣ አካላዊ ትድግናን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ያውላቸዋል፣ ጳውሎስ ከወኅኒ ቤት እንደ ዳነው ያለ (ፊሊጵስዩስ 1፡19)። እጅግ ተዘውትሮ፣…

ጥያቄ፤

ደኅንነት ምንድነው? የክርስቲያን ዶክትሪን ስለ ደኅንነት ምንድነው?

መልስ፤

ደኅንነት ከአደጋ ወይም ከመከራ መውጣት/መታደግ ማለት ነው። ማዳን፣ መታደግ ወይም መጠበቅ ማለት ነው። ቃሉ የድልን፣ የጤንነትን፣ ወይም የመጠበቅን ሐሳብ ይዟል። አንዳንድ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የዳነ ወይም ደኅንነት የሚሉትን ቃላት ጊዜያዊ፣ አካላዊ ትድግናን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ያውላቸዋል፣ ጳውሎስ ከወኅኒ ቤት እንደ ዳነው ያለ (ፊሊጵስዩስ 1፡19)።

እጅግ ተዘውትሮ፣ “ደኅንነት” የሚለው ቃል የሚያስረግጠው ዘላለማዊ፣ መንፈሳዊ ትድግናን ነው። ጳውሎስ ለፊሊጵስዩሱ ወኅኒ ቤት ጠባቂ ለመዳን የግድ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲነግረው፣ እሱ ያመለከተው ስለ ወኅኒ ጠባቂው ዘላለማዊ መዳረሻ ነው (ሐዋ. 16፡30-31)። ኢየሱስም በተመሳሳይ መልኩ መዳን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት መሆኑን ገልጿል (ማቴዎስ 19፡24-25)።

እኛ የዳንነው ከምንድነው? በክርስቲያን የደኅንነት ዶክትሪን፣ የዳንነው “ከቁጣው” ነው፣ ማለትም፣ ከእግዚአብሔር የኃጢአት ፍርድ (ሮሜ 5፡9፤ 1 ተሰሎንቄ 5፡9)። ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር ለይቶናል፣ የኃጢአትም ዋጋው ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)። መጽሐፍ ቅዱሳዊው ድኅነት/መዳን የሚያመለክተው ከኃጢአት ዋጋ መዳናችንን ነው፣ እና ስለዚህ የኃጢአትን መወገድ ያካትታል።

ማነው መዳንን የሚያደርገው? እግዚአብሔር ብቻ ነው ኃጢአትን ማስወገድ የሚችለው፣ እና ከኃጢአት ቅጣት የሚታደገን (2 ጢሞቴዎስ 1፡9፤ ቲቶ 3፡5)።

እግዚአብሔር እንዴት ያድናል? በክርስቲያን የድኅነት/መዳን ዶክትሪን፣ እግዚአብሔር በክርስቶስ አድኖናል (ዮሐንስ 3፡17)። በተለይም፣ የኢየሱስ የመስቀል ሞት፣ እና ተከትሎም በትንሣኤው ነው መዳናችንን ያገኘነው (ሮሜ 5፡10፣ ኤፌሶን 1፡7)። ቅዱስ ቃሉ ግልጽ ነው፣ ማለትም ደኅንነት ጸጋ ነው፣ የማይገባን የእግዚአብሔር ስጦታ (ኤፌሶን 2፡5፣ 8) እናም እሱም ሊገኝ የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ብቻ ነው (ሐዋ. 4፡12)።

ድኅነትን እንዴት መቀበል እንችላለን? የዳንነው በእምነት ነው። በቅድሚያ፣ ወንጌልን መስማት አለብን – የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ መልካም የምስራች (ኤፌሶን 1፡13)። እንግዲያውስ፣ ልናምን ይገባል – ጌታ አየሱስን ሙሉ ለሙሉ (ሮሜ 1፡16)። ይኽም ንስሐን፣ ስለ ኃጢአት እና ክርስቶስ የአስተሳሰብ ለውጥን ያካትታል (ሐዋ. 3፡19)፣ እናም የእግዚአብሔርን ስም መጥራትን (ሮሜ 10፡9-10፣ 13)።

የክርስቲያን ድኅነት/መዳን ዶክትሪን ፍቺ ሊሆን የሚችለው “በእግዚአብሔር ጸጋ መዳን፣ በኃጢአት ምክንያት ስለሆነው ዘላለማዊ ቅጣት፣ እሱም እግዚአብሔር ያስቀመጣቸውን ሁኔታዎች ማለትም ንስሐ እና ጌታ ኢየሱስን በማመን፣ በዚህም በእምነት ለተቀበሉት ተጠብቆላቸዋል።” ድኅነት/መዳን የሚገኘው በኢየሱስ ብቻ ነው (ዮሐንስ 14:6፤ ሐዋ. 4:12) እናም የሚወሰነው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፣ ለጥበቃ፣ ለዋስትና፣ እና ለደኅንነት።

[English]



[ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ]

ደኅንነት ምንድነው? የክርስቲያን ዶክትሪን ስለ ደኅንነት ምንድነው?

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.